banner

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ሕልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገለጹ

​#FastMereja I የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በታዋቂው አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ድንገተኛ ሕልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የኀዘን መግለጫ፣ አርቲስቱ ለሀገሩ የነበረውን አስተዋጽኦ በዝርዝር አውስተዋል።
​
​ጠቅላይ ሚኒስትሩ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በተለይም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ተዘጋጅቶ በነበረው የ2016 ዓ.ም አዲስ ዓመት መቀበያ መርሃ-ግብር ላይ የነበረውን ከፍተኛ ተሳትፎ አስታውሰዋል። “ነጻነት በዚያ ታሪካዊ ፕሮግራም ላይ የነበረውን አስተዋጽዖ ሁሌም አስታውሰዋለሁ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አርቲስቱ ኢትዮጵያውያን አዲሱን ዓመት በደስታና በተስፋ እንዲቀበሉ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና እንደነበረው ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይ፣ በአርቲስቱ ድንገተኛ ሞት ኀዘን ለደረሰባቸው፡
​ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣
​ለቅርብ ጓደኞቹ እና
​ለመላው አድናቂዎቹ
​ጽናትንና መጽናናትን ተመኝተዋል።

Leave a Comment