banner

ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ መንሱር ጀማል የት ነው?

#FastMereja I በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉትና በተለያዩ አነጋጋሪ ተግባራቱ የሚታወቀው መንሱር ጀማል፣ ከኢትዮጵያ ወጥቶ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪና ፋሶ እንደሚገኝ ታወቀ።

መንሱር ጀማል ከሀገር ከወጣ ሁለት ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ የቆይታ ቦታው መታወቅ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

መንሱር በድንገት ከሀገር መውጣቱን ተከትሎ የተለያዩ መላምቶች እየተሰነዘሩ ይገኛሉ። አንዳንዶች “ለስራ ጉዳይ ነው” ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ “እየሸሸ ነው” የሚሉ ያልተረጋገጡ ወሬዎችን እያናፈሱ ይገኛሉ። በተለይም በቲክቶክና በፌስቡክ መድረኮች ላይ ተከታዮቹ የት መሄዱንና ለምን መሄዱን በተመለከተ እርስ በእርስ እየተከራከሩ ነው።

መንሱር በአሁኑ ሰዓት በቡርኪና ፋሶ እንደሚገኝ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ይህች ሀገር ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ ለኢትዮጵያውያን የንግድም ሆነ የቱሪስት መዳረሻ ተደርጋ የማትታወቅ በመሆኗ የጉዞው አላማ ይበልጥ አጠራጣሪና አነጋጋሪ እንዲሆን አድርጎታል።

📌 ተከታዮቹ፦ “መንሱር በቅርቡ ትልቅ ሰርፕራይዝ ይዞ ይመጣል” በሚል በተስፋ እየጠበቁት ይገኛሉ።
📌 ተቺዎቹ፦ ከሀገር መውጣቱን በጥርጣሬ የሚመለከቱት ደግሞ “ያልተነገሩ እውነታዎች ሊኖሩ ይችላሉ” በማለት መረጃ እየተጠባበቁ ነው።

መንሱር ጀማል በቅርቡ በገጹ በኩል ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም፣ እስካሁን ግን ስለቆይታውና ወደ ሀገር ስለሚመለስበት ጊዜ በይፋ ያለው ነገር የለም።

10 comments

Ethio Joy January 20, 2026 - 10:21 am

Very funny! ….. Is loading!

Reply
Eyob Tilahun January 20, 2026 - 10:24 am

Very Funny

Reply
Nafol T Abdisa January 20, 2026 - 10:25 am

Because FinTech was under investigation 🙄

Reply
Eshetu Bekele Ye Barku January 20, 2026 - 10:27 am

Minase Wako Gudeta ጠይቁት

Reply
Qaroo Tesfaye January 20, 2026 - 10:27 am

Hawera 🤣✌️

Reply
Rabbirraa Lammii Galataa January 20, 2026 - 10:27 am

እዚህ ነው የእነሱን ፎቶዎች አይቻለሁ

Reply
Rahel Aklilu January 20, 2026 - 10:27 am

ቲክታክ ላይ አለልህ ከፈለከው ማለቴ ነው ግን ተፅኖ ገጣሪ ነው ያልከው?

Reply
Eleni Gonfa January 20, 2026 - 10:27 am

በጣም አሳስቦን ነበር

እባካችሁ ፈልጉልን

Reply
ማሴ የመሲ ልጅ January 20, 2026 - 10:28 am

ምን አገባኝ

Reply
Shimelis W Sileshi January 20, 2026 - 10:28 am

በጭንቀት ልናልቅ ነበር

Reply

Leave a Comment