banner

ታዋቂው የፊልም ባለሙያ ቴዎድሮስ ተሾመ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት 2ኛ ደብዳቤ ላከ

#FastMereja I ታዋቂው የፊልም ዳይሬክተር እና ፕሮዲዩሰር ቴዎድሮስ ተሾመ፣ የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ለሰጡት መግለጫ ምላሽ የሚሆን “ሁለተኛ ግልጽ ደብዳቤ” ለዋይት ሃውስ ልከዋል። ቴዎድሮስ በደብዳቤው ፕሬዝዳንቱ ስለ ግድቡ አመጣጥ እና ስለ ዓባይ ወንዝ ያላቸውን አመለካከት በጠንካራ ቃላት ተችቷል።

“ግድቡን አሜሪካ ከሰራችው ደረሰኝ ይላክልን”

ፕሬዝዳንቱ “ግድቡን አሜሪካ ነው የገነባችው” ማለታቸውን ያስታወሰው ቴዎድሮስ፣ ይህ እውነት ከሆነ ኢትዮጵያ ለግንባታው ያወጣችውን ወጪ እንድትመለስላት ጠይቋል። “ግድቡ የተገነባው በኢትዮጵያውያን ላብ እና ብር ነው፤ አንድም የአሜሪካ ደረሰኝ ወደ እኛ አልመጣም” ሲልም የግንባታውን የገንዘብ ምንጭ አስረድቷል።
ኢትዮጵያውያን በየካፌው የልገሳ ሳጥን በማዞር፣ ቦንድ በመግዛትና ከድሃው ጉሮሮ በመቀነስ “ተስፋቸውን በቅድሚያ የገዙበት” ፕሮጀክት መሆኑን በደብዳቤው ገልጿል።

“ዓባይ ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው”

ፕሬዝዳንቱ ዓባይን “ትንሽ ወንዝ” ማለታቸውን የተቸገረው ቴዎድሮስ፣ “ዓባይ ትንሽ ከሆነ ኤቨረስት ኮረብታ ነው፣ አንበሳም ድመት ነው” በማለት ወንዙ ለኢትዮጵያ ያለውን ታላቅ ትርጉም አብራርቷል።

ግብፅ ለቱሪዝም እና ለመዝናኛ ውሃ ያስፈልጋታል መባሉን በመቃወም፣ ግማሹ የኢትዮጵያ ህዝብ በጨለማ እንደሚኖርና ግድቡ ለኢትዮጵያውያን የSurvival (የህልውና)፣ የሃይል እና የክብር ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል።

“አሜሪካ በራሷ መሬት ላይ የገነባችውን የሁቨር ግድብ (Hoover Dam) አጠቃቀም በተመለከተ ከሜክሲኮ ትዕዛዝ ትቀበላለች ወይ?” የሚል ጥያቄ በማንሳት የኢትዮጵያን በራሷ ሃብት የመጠቀም መብት አስታውሷል።

በመጨረሻም፣ “ታላቁ የህዳሴ ግድብ በትዕግስት የጨረሱ የለፋ ህዝቦች መታሰቢያ እንጂ የአሜሪካ የቸርነት ፕሮጀክት አይደለም” ሲል ደብዳቤውን አጠቃሏል።

10 comments

Tekli Nguse January 21, 2026 - 7:39 pm

Who is he😁😁😁😁

Reply
Afomiya Kebron January 21, 2026 - 7:41 pm

Thank you

Reply
Michael Deyu Jima January 21, 2026 - 7:42 pm

አታስቀኛ! After part 10, he will convert it to movie as he has the potential to do so! ባይሆን let him make a movie about Nile river and what it means to Ethiopians. But this is senseless move.

Reply
Salih Alfayya January 21, 2026 - 7:43 pm

✅ MYTHS vs FACTS
1. “The U.S. paid for the dam.” ❌
FALSE. GERD is 100% financed by Ethiopians through public contributions and bonds.
2. “The dam stops the Nile.” ❌
FALSE. Hydropower does not consume water — it only regulates flow.
3. “Ethiopia blocked Egypt’s water.” ❌
FALSE. Water flow continued during filling, and downstream reservoirs remained full.
4. “The Nile belongs to Egypt.” ❌
FALSE. Ethiopia contributes over 86% of Nile waters. Modern diplomacy is based on fairness, not colonial-era claims.
5. “GERD is a crisis.” ❌
FALSE. Providing electricity to 65 million people is development, not a crisis.
6. “Ethiopia needed permission to build it.” ❌
FALSE. Nations do not need approval to use resources within their own borders.
7. “GERD is a weapon.” ❌
FALSE. It generates clean energy, prevents floods, and stabilizes drought impacts.
8. “GERD threatens Egypt’s survival.” ❌
FALSE. Egypt’s water challenges stem from management and climate change, not Ethiopia.
9. “A powerful outsider can solve this.” ❌
FALSE. Solutions come from cooperation among basin countries, not foreign pressure.
10. “Ethiopia should apologize for developing.” ❌
FALSE. Development is a human right — no apology needed.
🔹 CONCLUSION (Bottom Section)
GERD is not a threat — it is a solution.
Misinformation blocks a future where all Nile Basin countries win together.

Reply
Beyond Pardon January 21, 2026 - 7:44 pm

ጅል

Reply
Greta Hunter January 21, 2026 - 7:44 pm

😂😂😂😂በፖስታ ነው ወይስ በምንድን ነው ደብዳቤው የተላከው???? ነጭ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት ይጀመር💪 ስፖንሰር ጋሻው መርሻ😂😂😂😂😂። ደብዳቤውን ፀሀፊ ዳንኤል ክብረት ።

Reply
Genzebe Garo January 21, 2026 - 7:45 pm

የሶየው ጤና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ያለ ይመስለኛል።

Reply
Mam Yichalal Mire January 21, 2026 - 7:45 pm

Wow eg/ r yist ma nigerew leza jil

Reply
አረጋ የሀበሻ ልጅ January 21, 2026 - 7:45 pm

አይይ ጂል ሲጃጃል እቃ ይፈጃል አሉ

Reply
Abel Ahmed January 21, 2026 - 7:45 pm

ሪመምበር የቬንዙላን መሪ😂😂😂

Reply

Leave a Comment