#FastMereja : የማንበላዉን አንሸጥም በሚል መሪ ቃል ታፑ ሬስቶራንት እና ኮፊ በሜክሲኮ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት ፎቅ ላይ 2ተኛውን የሬስቶራንት ቅርንጫፉን በዛሬዉ እለት አስመርቋል።
የታፑ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ የምስራች አበራ በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር “ታፑ የአገር ባህል ምግቦች ለውጪ ገበያ ለማቅረብ የኤክስፖርት ፈቃድ አውጥተናል፤ የድርጅታችንን ብራንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስመዝገብ ላይ ነን ሲሉ ተናግረዋል።
አሁን ላይ ለህብረተሰቡ ዘርፎቹን በማስፋት 14 ቅርንጫፍ እና 2 የካፌ እና የሬስቶራንት አገልግሎት ለመስጠት በቅቷል።
በዛሬዉ እለት የተመረቀዉ ሬስቶራንት የተለያዩ የአገር ባህል ምግቦችን፣ ቡናን ጨምሮ የተለያዩ ትኩስ መጠጦች ለተገልጋዩ ህብረተሰብ እንደሚቀርብ ተገልጿል።
የድርጅቱ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ማርቆስ አበራ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች፣ የቱሪስት መስዕብ በሆኑ የአገራችን ፓርኮችና በውጭ አገራት ደረጃቸውን የጠበቁ የአገራችንን የምግብ ባህል አጉልተው የሚያሳዩ ሬስቶራንቶችን ለመክፈት እየሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ታፑን ወ/ሮ የምስራች አበራ መጋቢት 2ዐዐዐ ዓ.ም ጦር ሃይሎች ድልድይ አካባቢ በትንሽ ሱቅ ውስጥ ሳምቡሳ እና አምባሻ በመሸጥ የጀመሩት ቢዝነስ ሲሆን በአሁን ሰአት አድጎ ከ400 በላይ ሰራተኞች የሥራ ዕድል ፈጥሯል።




