0
#FastMereja I የሕወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ የፌደራል መንግሥቱ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በመጣስ ወረራ ለመፈፀም የጦር ኃይልና መሣሪያ ወደ ትግራይ ድንበር እያስጠጋ ነው አሉ።
ሊቀመንበሩ የድርጅቱን 51ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል (የካቲት 11) አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ መንግሥት በሰራዊቱና በሕዝቡ ላይ ተኩስ መክፈቱንና “አድቅቀናቸዋል፣ አሁንም እናደቅቃቸዋለን” የሚሉ የፕሮፓጋንዳ ዛቻዎችን እያሰማ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዓሉ የሚከበረው የሰላም ስምምነቱ በተጣሰበትና የወረራ ስጋት ባለበት ወቅት መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ደብረፅዮን፤ የትግራይ ሕዝብ ለሕልውናውና ለሉዓላዊነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲዘጋጅና እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል።
