banner

የቲክቶክ መንደር አነጋጋሪው ፍጥጫ፡ ጆን ዳንኤል እና ጃኒ በከባድ ክስ ተፋጠጡ!

#FastMereja I ​በቲክቶክ መንደር ከፍተኛ ተወዳጅነትን አትርፈው የነበሩት የቀድሞ ፍቅረኛሞች ጆን ዳንኤል እና ጃኒ በመካከላቸው ያለው አለመግባባት ተካሮ ወደ ከባድ ወንጀል ክስ ተሸጋግሯል። ጃኒ ዛሬ ባወጣችው ቪዲዮ በጆን ላይ ያቀረበችው ክስ እና ጆን የሰጠው ምላሽ በኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዘንድ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል።

​📌 የጃኒ ክስ፡ “ይደበድበኝ ነበር፤ አካውንቴንም ያዘጋው እሱ ነው”

​ጃኒ ዛሬ ባጋራችው ቪዲዮ ላይ በፍቅራቸው ወቅት በጆን ዳንኤል ከፍተኛ የአካል እና የሥነ-ልቦና ጥቃት (Abuse) ይደርስባት እንደነበር በዝርዝር ገልጻለች። በተጨማሪም፦
​”በፍቅር አብረን በነበርንበት ወቅት ይደበድበኝ ነበር” ስትል የቆየ በደሏን አውጥታለች።
​አሁን ላይ የቲክቶክ አካውንቷ እንዲዘጋ ያደረገው ጆን ዳንኤል እንደሆነ በድፍረት ከሳለች።

​📌 የጆን ዳንኤል ምላሽ፡ “ልጄን ይንሳኝ… ነክቻት አላውቅም!”

​ጆን ዳንኤል ክሱ በወጣ በደቂቃዎች ውስጥ ከ 100 ሺህ በላይ ተመልካቾች በታደሙበት የቀጥታ ስርጭት (Live) ቀርቦ ክሱን አጣጥሏል። ጆን በንግግሩ ውስጥ፦
​”ልጄን ይንሳኝ፣ እናት እና አባቴን ይንሳኝ እኔ ነክቻት አላውቅም” በማለት በቤተሰቦቹ ስም ምሏል።
​ጃኒ እራሷን የመጉዳት (Self-harm) ዝንባሌ እንዳላት በመግለጽ፣ “ከዚህ በፊት እንለያይ ስትለኝ እጇን በቢላ ስትቆርጥ ነበር፤ አስጥያት ነበር” ሲል ምስክር ነው ያለውን ፎቶ ለተመልካቾች አሳይቷል።

​📌 ጃኒ ለምን ላይቭ አልገባችም?

​ብዙዎች ጃኒ በቀጥታ ስርጭት ቀርባ ምላሽ ትሰጣለች ብለው ቢጠብቁም፣ እሷ ግን “ዛሬ ላይቭ አልገባም” በማለት በአካውንቷ ላይ መልዕክት በማስቀመጥ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥባለች። ይህ መቆጠቧ ደግሞ ተከታዮቻቸው መሃል የተለያዩ ጥርጣሬዎችን እና መላምቶችን እንዲፈጥሩ ምክንያት ሆኗል።

​የእኛ አስተያየት፡ የፍቅር ግንኙነቶች ወደ ጥላቻ እና ወደ ከባድ ክስ ሲቀየሩ ማየት የተለመደ ቢሆንም፣ የአካል ጥቃት እና እራስን የመጉዳት ሙከራዎች ግን በዝምታ ሊታለፉ የማይገቡ ጉዳዮች ናቸው። እውነቱ በሂደት የሚጣራ ቢሆንም፣ ለሁለቱም ወገኖች የሚዲያ ስነ-ምግባርን መከተልና በህግ አግባብ መጨረስ እንደሚበጅ የሾውቢዝ ዘገባችን ያሳስባል።

Leave a Comment