0
#FastMereja I ኢዜማ ወደ ዲጂታል አማራጮች በማዞር በቲክቶክ መድረክ ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል። ፓርቲው የሚለቃቸው አጫጭርና ፈጣን መልዕክቶች በተለይ በወጣቱ ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆነዋል።
ፓርቲው ከዚህ ቀደም ከሚታወቅበት ረጅም መግለጫና የቪዲዮ ስርጭት ወጥቶ፣ የቲክቶክን ባህሪ የተከተሉ አጫጭርና ግልጽ መልዕክቶችን መጠቀሙ ለተደራሽነቱ ረድቶታል።
ይህ የኢዜማ አካሄድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከባህላዊው የመገናኛ ዘዴ ወጥተው የነገ ሀገር ተረካቢ የሆነውን ወጣት በቅርበት ለማግኘት እያደረጉት ያለውን ሽግግር ያሳያል። የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ፓርቲው የያዘው ስትራቴጂ በሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ላይም ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ይገመታል።
