0
#FastMereja I የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ወቅት በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል አከራካሪ በሆኑ አምስት የምርጫ ክልሎች ላይ የሚከናወነውን የምርጫ ሂደት በተመለከተ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተላለፈለትን ውሳኔ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታወቀ።
ውሳኔው የሚያካትታቸው አካባቢዎች የሁመራ፣ የአዲረመፅ፣ የኮረም አፍላ፣ የጠለምት እና የራያ አላማጣ የምርጫ ክልሎችን ነው።
በእነዚህ አምስት የምርጫ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄው እስኪፈታ ድረስ፣ ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውጪ ሆነው ለብቻቸው በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ለፌዴራል) ብቻ ምርጫ እንዲካሄድ ተወስኗል።
በእነዚህ አካባቢዎች የሚደረገው የክልል ምክር ቤት ምርጫ ግን በአሁኑ ወቅት በአካባቢዎቹ ላይ ያለው የይገባኛል ውዝግብ በሕገ-መንግሥታዊ መንገድ ተፈትቶ አመቺ ጊዜ እስኪገኝ ድረስ ወደፊት እንዲካሄድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት መወሰኑ ተገልጿል።
#ፖለቲካ መረጃ
