0
#FastMereja I በኪይ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን (Key Housing Finance Solution) ውስጥ በባለአክሲዮንነት እና በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ግሩም ይልማ፣ ከዛሬ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን አስታወቁ።
በተቋሙ ውስጥ ሊኖሩ ስለሚገቡ የአሠራር ግልጽነት፣ የፋይናንስ ቁጥጥር እና የአባላትን ንብረት ስለመጠበቅ ያቀረቧቸው ተከታታይ የማሻሻያ ጥያቄዎች ምላሽ አላገኙም ብሏል።
በተለይም በአባላት መዋጮ የተገኘ ንብረት ለድርጅቱ የብድር ዋስትና (Collateral) ተደርጎ እንዳይወሰድ በግልጽ ቢቃወሙም ሰሚ በማጣታቸው ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።
ድርጅቱን አምነው ጥሪታቸውን ላስያዙ ደንበኞች የገቡትን ቃል ለመጠበቅ እና መብታቸውን አደጋ ላይ በሚጥሉ ጉዳዮች ላይ ላለመደራደር መወሰናቸውን ጠቅሰዋል።
አቶ ግሩም ከሥራ አስፈጻሚነት ቢለቁም፣ የድርጅቱ 20% ባለአክሲዮን በመሆናቸው የአባላትን መብት ለማስከበር ሕግ የሰጣቸውን መብት መጠቀማቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
