0
#FastMereja I የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አወዛጋቢ በሆኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ በጊዜያዊነት እንዲታገድ ትእዛዝ ሰጠ።
ፍርድ ቤቱ ይህንን ትእዛዝ ያስተላለፈው የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ የተባለው ፓርቲ ተወካይ አቶ ጌታቸው ረዳ ካቀረቡት አቤቱታ በኋላ ነው።
ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ከመረመረ በኋላ ምርጫ ቦርድ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል አወዛጋቢ በሆኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ክርክሩ ታይቶ እስኪያልቅ ድረስ በፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 154 መሠረት ታግዶ እንዲቆይ ታዟል።
ከሳሽ ያቀረበው ክስና ማስረጃ ለተከሳሽ (ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ) እንዲደርሰውና ተከሳሹ ለየካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 8፡30 ሰዓት መልሱን ይዞ እንዲቀርብ ታዟል።
#ፖለቲካ መረጃ
