#FastMereja I ሳሌም የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር የሌሎች ሀገራትን ስኬታማ ተሞክሮ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ያጣጣመ የጥናት ሰነድ በማቅረብ ይፋዊ የሥራ ማስጀመሪያ ፕሮግራሙን ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አካሄደ።
በዚህ መርሐ-ግብር ላይ፤ ማህበሩ በጀርመን፣ በአይርላንድ እና በኬንያ ያሉ ምርጥ የብድርና ቁጠባ ተሞክሮዎችን በመቀመር፣ አባላቱን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርግ አሠራር መዘርጋቱ ተገልጿል። ይህም ማህበሩ በዕውቀትና በጥናት ላይ ተመስርቶ ሥራ መጀመሩን የሚያሳይ መሆኑ ተመልክቷል።
የህብረት ሥራ ማህበሩ ሊቀመንበር ኢንጂነር በቃሉ ቢምረው በወቅቱ እንደገለጹት፤ “የሳሌም ዋና ዓላማ አባላትን የቁጠባ ባለቤት ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ በዝቅተኛ ወለድ የሚቀርብ ብድርን በመጠቀም የአባላትን የኑሮ ደረጃ ማሻሻልና ለሀገር ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል ነው” ብለዋል።
ማህበሩ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን የገለጸ ሲሆን፤ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል የማህበሩ አባል በመሆን የቁጠባ ባህሉን እንዲያሳድግ ጥሪ አቅርቧል።
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ሜክሲኮ ዬቤክ ህንፃ የቢሮ ምርቃት ተከናውኗል።
#ቢዝነስ ዘገባ




