#FastMereja I ዘማይ ኢምፖርት ኤክስፖርት በኢትዮጵያ አዲስ የሆነውንና በራሱ መኪኖችና አሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚሰጠውን “ዘማይ ጉዞ” የተሰኘ የሜትር ታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀምር ዛሬ የካቲት 25/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ማዶ ሆቴል በሰጠው መግለጫ በይፋ አስተዋውቋል።
በአሁኑ ወቅት 1,680 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለሥራ ዝግጁ ማድረጉን የዘማይ ጉዞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ የትናየት ሺበሺ ገልጸዋል።
አገልግሎቱ እንደ ደንበኛው ምርጫ ኢኮኖሚ፣ ቪአይፒ እና ዲፕሎማት ተብለው በሦስት ደረጃዎች ተከፍለዋል። የመነሻ ዋጋ 100 ብር ሲሆን፣ በኪሎሜትር ደግሞ 12 ብር ሆኖ ተቆርጧል። ይህም ለተጠቃሚው እጅግ አዋጭ ያደርገዋል ተብሏል።
ዘማይ ጉዞ የራሱ የሆነ የገመድ አልባ (Wireless) የቻርጅ ስቴሽን፣ ዘመናዊ ጋራዥ እና ስቲም መኪና ማጠቢያ አገልግሎቶችን አሟልቶ ይገኛል።
ዘማይ ጉዞ ለበርካታ ዜጎች አዲስ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል። “ዘማይ” የሚለው ቃል በራያ አካባቢ “አማች” ማለት እንደሆነ ተገልጿል።
ዘማይ ጉዞ በቅርቡ ወደ አገልግሎት እንደሚገባ ተነግሯል።
#ሳይ_ቴክ #ቢዝነስ




