banner

አዋሽ ባንክ 25 ሚሊዮን ብር በመለገስ የኢፍጣር መርሃ-ግብር አካሄደ።

#FastMereja I ​አዋሽ ባንክ የ1447ኛውን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ፣ “ከአዋሽ ለወዳጅ” በሚል መሪ ቃል በሸራተን አዲስ ሆቴል ታላቅ የኢፍጣር መርሃ-ግብር ዛሬ አካሄደ።
​
በጤና እና ማህበራዊ ዘርፍ ለሚሰሩ 7 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች 25 ሚሊዮን ብር ለግሷል። በሀገር አቀፍ ደረጃ በ52 ከተሞች ለሚገኙ 2,600 አባወራዎች፣ አረጋውያን እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖች የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

​​ባንኩ ከ1,005 በላይ በሆኑ ቅርንጫፎቹ 3.5 ሚሊዮን የኢክላስ ደንበኞችን ማፍራት ችሏል። ​ለወጣቶች እና ለኢንተርፕራይዞች (SMEs) ከ 25 ቢሊዮን ብር በላይ የሃላል ፋይናንስ አገልግሎት አቅርቧል።

​በሐጅ አገልግሎትም የውጭ ምንዛሬ በማቅረብ እና ክፍያዎችን በማሳለጥ መሪነቱን ዳግም አረጋግጧል።
​አዋሽ ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት ባለፈ፣ ሸሪዓን መሰረቱን ያደረጉ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረጉን እንደሚቀጥል የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በመርሃ ግብሩ ላይ ተናግሯል።

#ልዩ_ልዩ





Leave a Comment