0
#FastMereja | የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን፣ በኢራን ጥቃት ምክንያት በደረሰ የፍንዳታ ስብርባሪና ሽራፕኔል ቆስለው በሆስፒታል ህክምና ላይ የሚገኙ ተጎጂዎችን ጎበኙ።
ፕሬዝዳንቱ በሆስፒታል ተገኝተው የተጎጂዎችን የጤና ሁኔታ በቅርበት የተከታተሉ ሲሆን፣ ለተጎጂዎችና ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትንና ፈጣን ማገገምን ተመኝተዋል።
ተጎጂዎቹ የቆሰሉት በኢራን በኩል በተሰነዘረው ጥቃት ሳቢያ በተከሰቱ ፍንዳታዎችና ወደ መሬት በወደቁ የጥይትና የሚሳይል ስብርባሪዎች መሆኑ ተገልጿል።
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ መንግስታቸው ለዜጎቹና በሀገሪቱ ለሚኖሩ ነዋሪዎች ደህንነት ቅድሚያ እንደሚሰጥና አስፈላጊው የህክምና ድጋፍ ሁሉ እንዲደረግላቸው መመሪያ ሰጥተዋል።
