banner

ከእኔ ውጪ 400 ኢትዮጵያኖች ከአሜሪካ በቅርቡ ይባረራሉ

#FastMereja I አሜሪካ “የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽሟል” ያለችውን ግለሰብ ወደ ኢትዮጵያ አባረረች። ​የአሜሪካ ኢሚግሬሽን (ICE) ሰለሞን ቦጋለ የተባለውን ኢትዮጵያዊ “የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽሟል፣ በከባድ ወንጀልም ይጠረጠራል” በሚል በፈረንጆቹ መጋቢት 5 ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ማባረሩን አስታውቋል።

ግለሰቡ በትግራይ ተወላጆች ላይ የዘር ማጥፋት እና የማጽዳት እርምጃ እንዲወሰድ በማህበራዊ ሚዲያ ሲቀሰቅስ ነበር ተብሏል።

አክቲቪስቱ ሰለሞን ቦጋለ ከዘሀበሻ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ከአሜሪካ የተባረርኩት በሀሰት ዘመቻ ነው፣ በነበረው ጦርነት የኔ ጸብ ከህወሓት ጋር እንጂ ከትግራይ ህዝብ ጋር አይደለም “ጁ ንታ ይደምሰስ ብለሃል”፣ “ፋኖ ነኝ ብለሃል” ብለው ጥገኝነት ለመጠየቅ ፍርድ ቤት ቀጠሮ ነበረኝ እሱን ጨርሼ ስወጣ ነው ይዘው 2 ወር ያሰሩኝ ብሏል።

ሁለት አመት አሜሪካ የቆየው ሰለሞን የራሱን ትራክ ገዝቶ እየሰራ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የራሱን ድርጅት ከፍቶ እየሰራ ነበር።

ሰለሞን ብዙ ጥገኝነት እየጠየቁ ያሉ ኢትዮጵያኖች እየተባረሩ ነው በቅርቡ ወደ 400 ሰው ወደ ኢትዮጵያ ይባረራል ብሏል።

Leave a Comment