0
#FastMereja I በመካከለኛው ምሥራቅ እየተከሰተ ያለው ቀውስ በዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ነዳጅ አከፋፋዮች፣ ማደያዎችና ተጠቃሚዎች ያሉትን ሀብቶች በቁጠባ እንዲጠቀሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በመካከለኛው ምሥራቅ በተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ አገራት አቅርቦቱን እንደልብ ለማግኘት መቸገራቸውን ገልጸዋል። ይህ ዓለም አቀፋዊ ችግር ተፈትቶ አቅርቦቱ ወደ መደበኛ ሁኔታው እስኪመለስ ድረስ ያሉትን አማራጮች በአግባቡ ማስተዳደር እንደሚገባ አሳስበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ነዳጅን ለመሠረታዊና ለአስፈላጊ አገልግሎቶች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም እንደሚገባ አሳስበዋል። በአቅርቦት እጥረት ወቅት ብክነትን በማስወገድ በቁጠባ የመጠቀም አስፈላጊነት ነው ብለዋል። የነዳጅ አከፋፋዮች፣ የነዳጅ ማደያዎችና አጠቃላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ አቅርበዋል።
