banner

የነዳጅ አቅርቦት እጥረትን ለመቋቋም ነዋሪዎች የትራንስፖርት አማራጮችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ

​
#FastMereja I በመካከለኛው ምሥራቅ በተከሰተው ወቅታዊ ቀውስ ሳቢያ በዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት ላይ መስተጓጎል መፈጠሩን ተከትሎ፣ የከተማዋ ነዋሪዎች ነዳጅን በቁጠባ እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ።

​ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገራት በአሁኑ ወቅት አቅርቦቱን እንደልብ ለማግኘት ተግዳሮት እንደገጠማቸው ገልጸዋል። ይህ ችግር ተፈትቶ የነዳጅ አቅርቦቱ ወደ መደበኛ ሁኔታው እስኪመለስ ድረስ ህዝቡ አማራጭ መንገዶችን እንዲከተል አሳስበዋል።

​ነዋሪዎች የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ የሚከተሉትን እርምጃዎች እንዲወስዱ ተጠይቋል፦
​አጫጭር መንገዶችን በእግር መጓዝ፤
​የብስክሌት አማራጮችን በስፋት መጠቀም፤
​የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን (EV) ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም።

​ከንቲባዋ አክለውም፣ ወቅታዊው የነዳጅ እጥረት ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው መሆኑን በመገንዘብ ነዋሪው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በመጨረሻም “ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ” በማለት መልዕክታቸውን ደምድመዋል።

Leave a Comment