banner

ካፒታል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር በቤቴል ቅርንጫፍ መክፈቱን አስታወቀ

​#FastMereja I ካፒታል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማስፋፋት እና የወለድ አልባ አገልግሎትን ለደንበኞቹ ለማቅረብ የሚያስችለውን አዲስ ቅርንጫፍ በቤቴል ከፈተ።

​በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የማህበሩ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ደረጀ መኮንን፤ ማህበሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ሥራዎችን ማከናወኑን ጠቁመው፣ አዲሱ ቅርንጫፍ የአባላትን የቁጠባና ብድር ፍላጎት ለማርካት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

​የተቋሙ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጅሬኛ ነገሬ በበኩላቸው፤ “ቅርንጫፉ በአካባቢው ለሚገኙ አባላት ቀላልና ተመጣጣኝ የብድር አገልግሎት በመስጠት የኢኮኖሚ እድገት ላይ የራሱን አዎንታዊ አሻራ ያሳርፋል” ብለዋል። በምረቃው ላይ ከመንግስት ኮሚሽን የተጋበዙ እንግዶች፣ የማህበሩ አመራሮችና አባላት ተገኝተዋል።

#ቢዝነስ





Leave a Comment