banner

ሀሴት ሪፍሎክሶሎጂ በቦሌ አዲስ ማዕከል በይፋ አስመረቀ።

#FastMereja I በከተማችን ደረጃውን የጠበቀ የሪፍሎክሶሎጂ አገልግሎት በመስጠት የሚታወቀው ሀሴት ሪፍሎክሶሎጂ አዲስ ማዕከሉን በቦሌ ሪያሊቲ ፕላዛ 2ኛ ፎቅ ላይ ዛሬ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ አስመረቀ።

ይህ አዲስ ማዕከል ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎትና ቀላል ተደራሽነት ለማቅረብ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ተቋሙ በሙያዊ ስነምግባር የተመሰረተ ከፍተኛ ደረጃ ያለው አገልግሎት መስጠቱን ቀጥሏል።

የተቋሙ መስራችና ባለቤት ወ/ት ፅጌረዳ ወ/ዩሀንስ በንግግራቸው፣ ተቋሙ ለብዙ ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ሙያን በማክበር እና በፍቅር በመስራት ወጣቶች የሚፈልጉትን ደረጃ መድረስ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

በመጨረሻም ለአጋሮቻቸው ሼባ ቪሌጅስ ሆቴሎችና ሪዞርቶች፣ ሻሎም ሪፍሎክሶሎጂ፣ ሀምሌት ቴራፒ እና Th Group ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

#ቢዝነስ መረጃ





Leave a Comment