banner

የፊቼ ጫምባላላ በዓል በአዲስ አበባ በልዩ ድምቀት ተከበረ!

#Fastmereja I የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫና በዩኔስኮ (UNESCO) በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የፊቼ ጫምባላላ በዓል በዛሬዉ እለት በወዳጅነት አደባባይ በድምቀት ተከበረ።

በዓሉ በመዲናዋ ለ7ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን ዋና ዓላማውም የሰላም፣ የእርቅና የአንድነት እሴቶችን ለሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ማጋራት እንደሆነ ተገልፆ በዓሉ ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትና ለተፈጥሮም ጭምር ሰላምን የሚመኝ ጥልቅ ባህላዊ ትርጉም ያለው መሆኑም ተመላክቷል።

ፊቼ ጨምበላላ ትልቅ የመንፈሳዊና የቁሳዊ ባህል እሴት የሚታይበት በዓል መሆኑን እና፤ የጨረቃንና የከዋክብትን ፈለግና ዑደት ለዘመናት የቀመረ ነባር ሀገር በቀል የእውቀት መገለጫ መሆኑን አስረድተዉ በበዓሉ ላይ የሚታየው የባህሎች መስተጋብርም ኢትዮጵያ የምታልማትን የጋራና ማንነት የሚያንፀባርቅ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትርዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ገልፀዋል።

በዓሉ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ መሪነትና ድጋፍ በየዓመቱ እየተከበረ የቆየ ሲሆን፣ አሁን ላይ ለከተማዋ ተጨማሪ ድምቀት የሚሰጥ ትልቅ ህዝባዊ ፌስቲቫል ለመሆን መብቃቱ ነዉ የተገለፀዉ።

በዛሬዉ እለት በተከናወነዉ መርሀ-ግብር ላይ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሲዳማ ማህበረሰብ አባቶች፣ አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች እንዲሁም በርካታ የሲዳማ ተወላጆች ታድመዋል።

#ኹነት





Leave a Comment