#Fastmereja I ዘማይ ኃ.የተ.የግ.ማ ግዙፍና ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎቱን በዛሬዉ እለት በመስቀል አደባባይ ለህዝብ ይፋ አድርጓል።
ዘማይ ኃ.የተ.የግ.ማ በባለቤትነት የሚያስተዳድራቸው ዘማይ ጉዞ እና ዘማይ ብር በኢትዮጵያ የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ዘመናዊ፣ ምቹ እና ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት የሰጡ አዳዲስ አገልግሎቶችን መጀመራቸውን በዛሬዉ እለት በተካሄደ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ ተገለፀ።
ዘማይ ጉዞ ራሱ ባስመጣቸውና ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ በሚሰሩ 1,680 ተሸከርካሪዎች አገልግሎቱን የጀመረ ሲሆን፣ በቀጣይ የተሽከርካሪዎቹን ቁጥር ወደ 30,000 ለማድረስ ማቀዱንም ነዉ የገለፀዉ።
የአገልግሎቱ ልዩ ባህሪያት ተሳፋሪዎችን ማዕከል ያደረጉ ሲሆኑ፣ተሳፋሪ ንብረቱን ጥሎ ቢወርድ በሳይረን ጥቆማ የሚሰጥ እና መኪናው እንዳይንቀሳቀስ የሚቆልፍ (System Lock) ቴክኖሎጂ ፣ በጉዞ ወቅት ስልክን ያለገመድ መሙላት የሚያስችል (Wireless Charger) አገልግሎት እንዲሁም ተሽከርካሪዎቹን ከውሃና ከእርጥበት ንክኪ ለመጠበቅ እንዲሁም ጊዜን ለመቆጠብ በእንፋሎት (Steam Washing) የማጽዳት ዘዴን ያካተቱ መሆናቸዉ ተገልጿል።
ድርጅቱ የአገልግሎት ዋጋውን ማህበረሰቡን ባገናዘበ መልኩ ያቀረበ ሲሆን፣ የመነሻ ዋጋ 100 ብር ሆኖ በኪሎሜትር 12 ብር ብቻ እንደሚታሰብ አስታውቋል።
ከዚህም በተጨማሪ ክፍያዎችን ቀላል እና ዲጂታል ለማድረግ “ዘማይ ብር” የተሰኘ የክፍያ መተግበሪያ ስራ ላይ የዋለ ሲሆን የዘማይ ብር መተግበሪያን አውርደው ክፍያ የሚፈጽሙ ደንበኞች የ20% የዋጋ ቅናሽ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።
ዘማይ ኃ.የተ.የግ.ማ ትኩረቱ የንግድ ትርፍ ላይ ብቻ ሳይሆን ለሀገር ኢኮኖሚም ጭምር መሆኑን ተገልፆ ድርጅቱ በሰኮንድ እስከ 1 ሚሊዮን ጥሪዎችን ማስተናገድ የሚችል “6312” የተሰኘ ዘመናዊ የጥሪ ማዕከል ያቋቋመ ሲሆን፣ ይህም ለዜጎች ሰፊ የስራ እድል እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።
ዘማይ ኃ.የተ.የግ.ማ የቴክኖሎጂ እና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን በማቀናጀት የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ለማገዝ ቁርጠኛ መሆኑን በምረቃው ወቅት መልዕክቱን አስተላልፏል።
#ቢዝነስ መረጃ




