banner

ዛሬ የዶክተሮች ቀን ነው።

​#FastMereja I ዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም (March 30, 2026) በመላው ዓለም የሃኪሞች ቀን (Doctors’ Day) የህክምና ባለሙያዎች ለሰው ልጅ ህይወት መታደግ የሚያደርጉትን ተከታታይ ተጋድሎ በማሰብ በታላቅ ክብር እየተከበረ ይውላል።
​ይህ በየዓመቱ መጋቢት 21 ቀን የሚከበረው የሃኪሞች ቀን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንጆቹ 1933 በዊንደር ጆርጂያ መከበር የጀመረ ሲሆን፣ ዕለቱ የተመረጠውም ዶክተር ክራውፎርድ ደብሊው ሎንግ ለመጀመሪያ ጊዜ “ኢተር” (Ether) የተሰኘውን ማደንዘዣ ለህክምና አገልግሎት ያዋሉበትን አንደኛ ዓመት መታሰቢያ በማድረግ ነበር።

​በየደቂቃው በሚታደሱ የህክምና ግኝቶች ውስጥ ሆነው፣ ዕውቀታቸውንና ጉልበታቸውን መስዋዕት በማድረግ በታማሚዎችና በሞት መካከል ቆመው ለሚያገለግሉ የህክምና ባለሙያዎች ዕውቅና መስጠት የዕለቱ ዋነኛ ዓላማ ነው። ማህበረሰቡም በየደረጃው የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን “ስለ አገልግሎታችሁ እናመሰግናለን” በማለት የሞራል ድጋፍ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

Leave a Comment