banner

ኦስትሪያ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች የአየር ክልሏን እንዳይጠቀሙ ከለከለች፤ ዶናልድ ትራምፕ ኔቶን “የወረቀት አንበሳ” ሲሉ ተ

ኦስትሪያ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች የአየር ክልሏን እንዳይጠቀሙ ከለከለች፤ ዶናልድ ትራምፕ ኔቶን “የወረቀት አንበሳ” ሲሉ ተቹ

​#FastMereja | ኦስትሪያ በአሜሪካና በኢራን መካከል እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች የአየር ክልሏን እንዳይጠቀሙ መከልከሏን አስታወቀች። ሀገሪቱ ለውሳኔዋ እንደ ምክንያት ያቀረበችው የገለልተኝነት ፖሊሲዋን እና ግጭቱ እንዳይባባስ ያላትን ስጋት ሲሆን፣ ይህንኑ ተከትሎ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሰጡት መግለጫ ኔቶን “የወረቀት አንበሳ” ሲሉ አጣጥለዋል።

​በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት አውሮፓን ለሁለት እየከፈለ ይገኛል። ኦስትሪያ ይህን ውሳኔ ያሳለፈችው ከስፔን፣ ጣሊያን፣ ስዊዘርላንድ እና ፈረንሳይ በመቀጠል ሲሆን፣ እነዚህ ሀገራትም የአሜሪካ ጦር ለአየር ጥቃትም ሆነ ለትጥቅ ማጓጓዣ የአየር ክልላቸውን እና ወታደራዊ ካምፖቻቸውን እንዳይጠቀም በይፋ ከልክለዋል። በተለይም ስፔን የአየር ክልሏን ዝግ ማድረጓ እና ጣሊያን የአሜሪካ ጦር አውሮፕላኖች በሲሲሊ ደሴት እንዳያርፉ መከልከሏ በዋሽንግተን ላይ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።

​የአውሮፓ ሀገራት እያሳዩት ያለው ተቃውሞ ያስቆጣቸው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ “ኔቶ አሜሪካን ለብቻዋ እየተዋት ነው” በሚል የጥሬ ድምፅ ወርፈዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም አሜሪካ ከኔቶ አባልነቷ የምትወጣበትን ሁኔታ “በድጋሚ እያጤንኩት ነው” ሲሉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። በኢራን ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት ከተጀመረ አንድ ወር ያስቆጠረ ሲሆን፣ በኢራን በኩልም ለሚሰነዘሩ የአጸፋ እርምጃዎች ስጋት ያደረባቸው የአውሮፓ ሀገራት ከግጭቱ እጃቸውን ለማውጣት እየሞከሩ መሆኑ ተመልክቷል።

​ቅዳሜ፣ መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

Leave a Comment