#Fastmereja: ኦሮሚያ ባንክ የዘንድሮን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ7 የተለያዩ ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የ5 ሚሊዮን የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
በዚህ መርሃ ግብር ድጋፍ የተደረገላቸዉ ድርጅቶች:
1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን 1,000,000.00 ብር
2. አበበች ጎበና የበጎ አድራጎት ድርጅት 1,000,000.00 ብር
3. የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት 1,000,000.00 ብር
4. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምገባ ማዕከል 500,000.00 ብር
5. ኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤት 500,000.00 ብር
6. ተስፋ አዲስ፡ የህጻናት የካንሰር ህሙማን ማዕከል 500,000.00 ብር
7. ሰበታ የአይነ ስዉራን ትምህርት ቤት 500,000.00 ብር ድጋፍ ተደርጓል።
የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦቦ ተፈሪ መኰንን በድጋፍ መርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክ፣ ባንኩ የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ ሀገር በቀል ድርጅቶች ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉን አስታዉሰዉ፣ በዛሬዉ ዕለትም አብይ ጾምን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ማህበራዊ ችግር ያለባቸዉን ዜጎች የሚረዱ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችን የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።
በመጨረሻም የግብረ ሰናይ ድርጅቶቹ የስራ ኃላፊዎች እና ተወካዮች ባንኩ ላደረገላቸዉ ድጋፍ አመስግነዉ፣ ይህ ድጋፍ አኛ ለምንሰራዉ ሰብአዊ ስራ ትልቅ ስንቅ እና ማበረታቻ የሚሆነን ነዉ ብለዋል፡፡




