0
#FastMereja I የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ያቀረቡትን የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም የሰላም ጥያቄ፣ የኢራን መንግስት “በበጎ ሁኔታ” እየመረመረው መሆኑን አንድ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል ማክሰኞ ዕለት ገለጹ።
ይህ መረጃ የወጣው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥን እንድትከፍት የሰጡት ቀነ-ገደብ ሊያበቃ ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩት ነው። ኢራን ለጥያቄው አዎንታዊ ምላሽ የምትሰጥ ከሆነ፣ በቀጠናው የተደቀነውን መጠነ ሰፊ ጦርነት ለጊዜውም ቢሆን ሊገታው ይችላል ተብሎ ተስፋ ተጥሏል።
