0
#FastMereja I የላቲን አሜሪካዊቷ ሀገር ብራዚል፣ የበሬ፣ የዶሮ እና የአሳማ ሥጋን ጨምሮ 17 የግብርና ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ የሚያስችላትን ይፋዊ ፍቃድ ማግኘቷን የሀገሪቱ ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የብራዚል ግብርና ሚኒስቴር የንግድ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ፀሐፊ ልዊስ ሩዋ ለሮይተርስ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በ130 ሚሊዮን ህዝቧ ለብራዚል ምርቶች ትልቅና ወሳኝ ገበያ ናት። ይህ ስምምነት ባለፈው ሳምንት ሹመት ለተቀበሉት አዲሱ የግብርና ሚኒስትር አንድሬ ዲ ፓውላ የመጀመሪያው የገበያ ስኬት ተደርጎ ተወስዷል።
ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።
