#FastMereja I በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ በጤና ባለሙያው ዋቆ ከድር ላይ ከፍተኛ ድብደባ የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። ድርጊቱ የተፈጸመው ትላንት ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ዓ.ም በሮቤ ከተማ መነሃሪያ አካባቢ መሆኑ ተገልጿል።
የሮቤ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ገመዳ ቱሊቻ ለኦቢኤን እንደገለጹት፣ ለጥቃቱ መንስኤ የሆነው አንደኛው ተጠርጣሪ “ስልኬን ወስዶብኛል” በሚል ሰበብ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን በጤና ባለሙያው ላይ ጥቃት መፈጸሙ ነው። በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች አከለ አሰፋ፣ አብዲሳ ከድር፣ ቦንሳ አወል፣ መሐመድ ፋኖ እና ኢብራሂም ሁሴን የተባሉ ግለሰቦች መሆናቸው ታውቋል።
ጥቃቱ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት መነጋገሪያ የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ፖሊስ ጉዳዩን እያጣራ እንደሚገኝና አስፈላጊው የህግ እርምጃ እንደሚወሰድ ኮማንደር ገመዳ ገልጸዋል። ለግጭቱ መነሻ የሆነውና በአሁኑ ወቅት ተሰውሮ የሚገኘው ግለሰብ በቁጥጥር ስር እንዲውል ክትትል እየተደረገ መሆኑን ፖሊስ ጠቁሞ፣ ህዝቡ ጉዳዮችን ሳያጣራ በራሱ እርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠብ ጥሪ አቅርቧል።
ቅዳሜ ሚያዝያ 3 ቀን 2018 ዓ.ም.
ቪዲዮ ለማየት 📍https://t.me/fastmereja
