0
#FastMereja I የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ከበጎ አድራጎት ክለቦች ጋር በመተባበር በፊቼ ከተማ ለሚገኙ 16 አቅመ ደካማ ወገኖች የምግብ እና የዘይት ድጋፍ አደረጉ። ተማሪዎቹ ካላቸው ጥቂት ገቢ ላይ በማዋጣት ያሰባሰቡትን ድጋፍ የበዓል መዳረሻን ምክንያት በማድረግ ለተጠቃሚዎቹ አስረክበዋል።
የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ከጸረ-ሙስና፣ ከቀይ መስቀል እና ከሌሎች የዩኒቨርሲቲው ክለቦች ጋር በመቀናጀት ባከናወኑት የሰብዓዊ እርዳታ ተግባር፣ ለእያንዳንዱ ተጠቃሚ 5 ኪሎ ግራም ዱቄት እና ዘይት አበርክተዋል። ከምግብ ቁሳቁሱ በተጨማሪ ከተማሪዎች የተሰበሰቡ አልባሳት ለተቸገሩ ወገኖች መከፋፈላቸው ታውቋል።




