banner

የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሙስሊሙ ማህበረሰብ በምርጫው ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ

#FastMereja I የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ባስተላለፈው መመሪያ፤ እድሜው ለምርጫ የደረሰ እያንዳንዱ ሙስሊም የምርጫ ካርድ በመውሰድ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ አሳሰበ። ምክር ቤቱ “ዛሬ የምንሰጣት ድምጽ ነገ የመብት ጥያቄያችንን ትመልሳለች” ሲል የምዝገባው ወቅት ሳይጠናቀቅ ማህበረሰቡ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርቧል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኩል ዛሬ የወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው፣ ምርጫ መብትን ለማስከበርና ማህበራዊ ስርዓትን ለማስተካከል የሚያስችል ስልታዊ መሳሪያ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል። ህገ-መንግስታዊው የሀይማኖት እና የመንግስት መለያየት ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሀገሪቱ የፖለቲካ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የጎላ ድርሻ ሊኖረው እንደሚገባ ምክር ቤቱ አመልክቷል።

ምክር ቤቱ በመጨረሻም “መብት የሚረጋገጠው በነቃ ተሳትፎ ነው” በማለት፣ ለሀገርና ለህዝብ የሚበጅ ተመራጭ ለመምረጥ መመዝገብ የመጀመሪያው እርምጃ መሆኑን አስታውሷል።



Leave a Comment