banner

የቼልሲ እና የስትራስቡርግ ደጋፊዎች በብሉኮ (BlueCo) ባለቤትነት ላይ የተቃውሞ ድምፃቸውን በስታምፎርድ ብሪጅ አሰሙ

​#FastMereja I የቼልሲ እና የፈረንሳዩ ስትራስቡርግ ክለብ ደጋፊዎች በጋራ በመሆን የሁለቱ ክለቦች ባለቤት በሆነው “ብሉኮ” (BlueCo) ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ገለጹ። ደጋፊዎቹ “ባለብዙ ክለብ ባለቤትነት” (Multi-club ownership) የእግር ኳስን መንፈስ ይገድላል በሚል በጋራ አቋም መቆማቸው ተሰምቷል።

​በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው በዚህ የተቃውሞ መርሃ ግብር ላይ፣ የስትራስቡርግ ደጋፊዎች ወደ ለንደን በመጓዝ ከቼልሲ ደጋፊዎች ጋር ተቀላቅለዋል። ደጋፊዎቹ ይዘዋቸው በወጡት መፈክሮች የቶድ ቦህሊ እና የክሊርሌክ ካፒታል አስተዳደር በክለቦቹ ማንነት እና ታሪክ ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም የስትራስቡርግ ደጋፊዎች ክለባቸው የቼልሲ ማሳደጊያ እየሆነ ነው በሚል ከፍተኛ ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛሉ።

Leave a Comment