0
#FastMereja I የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ዛምቢያ ለማዕድን ሀብቷ ለአሜሪካ ኩባንያዎች ቅድሚያ የሚሰጥ አሰራር ካልዘረጋች፣ ለሀገሪቱ የምታደርገውን የጤና ፈንድ ከፍተኛ ቅናሽ እንደምታደርግ ማስጠንቀቂያ ሰጡ። የደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ዛምቢያ እስከ ፊታችን ሐሙስ ድረስ ውሳኔዋን እንድታሳውቅ ቀነ-ገደብ ተቀምጦላታል።
ይህ የአሜሪካ ጥያቄ ተቀባይነት ካላገኘ፣ በጤናው ዘርፍ ላይ የሚደረገው ድጋፍ ሊቋረጥ ይችላል። ይህም በዩኤስ የገንዘብ ድጋፍ የኤችአይቪ (HIV) ሕክምና የሚያገኙ 1.3 ሚሊዮን ዛምቢያውያን ሕይወት ላይ ከፍተኛ አደጋ እንደሚደቅን ተነግሯል።
ትራምፕ ይህን ግፊት እያደረጉ ያሉት አሜሪካ ስትራቴጂካዊ ለሆኑ ማዕድናት የምታገኘውን አቅርቦት ለማረጋገጥ በሚያደርጉት ጥረት እንደሆነ ቢገለጽም፣ ጉዳዩ በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል። ዛምቢያ በማዕድን አቅርቦት እና በዜጎቿ የጤና ዋስትና መካከል ከባድ ውሳኔ የሚጠብቃት ይሆናል።
