0
#FastMereja I በምዕራብ ሸዋ ዞን ደንዲ ወረዳ ትላንት ምሽት በደረሰ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ መገልበጥ አደጋ የ18 ሰዎች ሕይወት አልፏል። በአደጋው በርካታ መንገደኞች ላይም ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
በምዕራብ ሸዋ ዞን ደንዲ ወረዳ፣ ወርቃ ጋራ ቀበሌ “ጋራ ሆላ” ተብሎ በሚጠራው ልዩ ቦታ ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 1፡30 አካባቢ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ተከስቷል። ከአልፋታ ወረዳ ወደ ደንዲ ወረዳ በመጓዝ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ 3 OR 77305 የሆነ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከመንገድ ወጥቶ በመገልበጡ አደጋው መከሰቱን የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።
በአደጋው ሕይወታቸው ካለፈው 18 ሰዎች መካከል 13ቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ 5ቱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል። በተጨማሪም 13 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፣ 26 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፣ በአጠቃላይ በተሽከርካሪው ላይ የነበሩ 57 መንገደኞች ላይ የአካልና የሕይወት ጉዳት ደርሷል።
