0
#FastMereja I የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የለንደኑ አርሰናል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ የሚደረጉትን የአገሪቱን ደጋፊዎች የአደባባይ ደስታ አጣጣሉ። ፕሬዝዳንቱ አፍሪካውያን ከባህር ማዶ እግር ኳስ ይልቅ ትኩረታቸውን በስራ ፈጠራ፣ በልማት እና በድህነት ቅነሳ ላይ ማድረግ እንዳለባቸው በምሬት ገልጸዋል።
የአርሰናልን የዋንጫ ድል እንዲያከብሩ ከደጋፊዎች የቀረበላቸውን ጥሪ ውድቅ ያደረጉት ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ፣ ሰዎች ይህንን ድል እንዲያከብሩ መጠበቃቸው እንዳስገረማቸው በይፋ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ በሀገሪቱ ላይ አሁንም እልባት ያላገኙ በርካታ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ባሉበት ሁኔታ፣ ትኩረትን ወደ አውሮፓ እግር ኳስ ማዞር ተገቢ እንዳልሆነ አሳስበዋል። ይህ የፕሬዝዳንቱ ጠንከር ያለ አስተያየት በተለይም በአውሮፓ እግር ኳስ አፍቃሪ በሆኑት በርካታ የኡጋንዳ ወጣቶች እና በፖለቲካ ተንታኞች ዘንድ ሰፊ ክርክርና የሃሳብ መከፋፈልን ፈጥሯል።
