0
#FastMereja I የትግራይ መከላከያ ኃይል ተብሎ የሚጠራው TDF አካል የሆነው አርሚ 33 ፣ ለሶስት ሳምንታት ሲያሰለጥን የቆየውን አቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው ዕለት አጠናቀቀ። ስልጠናው በተለይም በውትድርና ሳይንስ፣ በቴክኒክ ብቃት እና ወቅታዊ የፖለቲካ ትንተናዎች ላይ ትኩረት ያደረገ እንደነበር ተገልጿል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአርሚ 33 አመራሮች፣ ስልጠናው የትግራይን የተወረረ ሉዓላዊ መሬት ለማስመለስ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እና በወረራ ስር የሚገኙ ወገኖችን ነጻ ለማውጣት የሚደረገውን ጥረት አቅም የሚገነባ መሆኑ ተገልጿል።



