#FastMereja በኬንያ ላይኪፒያ ግዛት ናኙኪ ከተማ የአሜሪካ መንግስት ሊገነባው ባቀደው የኢቦላ መከላከያ ማኳያ ማዕከል ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ዛሬ ሰኞ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ አደረጉ።
ነዋሪዎቹ የኢቦላ ቫይረስ ተጋላጭ የሆኑ አሜሪካውያንን ለማቆየት በኬንያ አየር ኃይል የጦር ሰፈር ውስጥ ሊገነባ የታቀደውን ባለ 50 አልጋ ማዕከል የተቃወሙት፣ አስቀድሞ ምንም ዓይነት የሕዝብ ውይይትና ምክክር ሳይደረግበት በምስጢር የተወሰነ ነው በሚል ነው።
ነዋሪዎችና ፖሊስ ወደ ግጭት ውስጥ የገቡ ሲሆን የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ሰልፈኞችን ለመበተን መገደዳቸው ታውቋል። በተፈጠረው ግርግር ሳቢያ የናኙኪ ከተማ የንግድና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የተስተጓጎለ ሲሆን፣ ማዕከሉ ሊገነባ ነው የሚለው ዜና የአካባቢውን የቱሪዝም ዘርፍ ክፉኛ መምታቱ ተገልጿል። በርካታ ዓለም አቀፍ ቱሪስቶች ወደ አካባቢው የሚያደርጉትን የሆቴልና የሆምስቴይ የቦታ ማስያዣ ጥያቄዎችን በጅምላ እየሰረዙ መሆኑን የዘርፉ ባለቤቶች በምሬት ተናግረዋል።
የአካባቢው የንግድ ምክር ቤትና የፖለቲካ መሪዎች መንግስትን በግልጽ እየተቹ ሲሆን፣ የአገሪቱ የጤና ሥርዓት መሰረታዊ ክትባቶችን እንኳን ማቅረብ ባልቻለበት ሁኔታ ዓለም አቀፍ አደጋ የሆነውን የኢቦላ ማቆያ ማዕከል መቀበል አደገኛ መሆኑን ገልጸዋል።




