banner

የእንጦጦ-ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ተመረቀ

​#FastMereja | የፊታችን ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 ቀን 2026 ዓ.ም፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተከናወነው የእንጦጦ-ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ተመርቆ ለሕዝብ ክፍት ሆኗል። ፕሮጀክቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቋል።

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት፤ ከዚህ ቀደም ለሰው ኑሮ ምቹ ያልሆነ፣ የተጎሳቆለ እና ለአደጋ የተጋለጠ የነበረው የእንጦጦ እስከ ቀጨኔ ያለው አካባቢ፣ አሁን ላይ ወደ ቀድሞ ተፈጥሯዊ ይዘቱ ተመልሶ ውብ እና ማራኪ ገጽታን ተላብሷል። ይህ ፕሮጀክት የከተማዋን “ሳምባ” በሆነው ደን ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ ታሪክ እና የስራ ባህል የሚያንጸባርቁ ቅርሶችና ሐውልቶች ተካተውበታል።

​የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ይዘቶች፦

ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 597 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፣ 9.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የወንዝ ዳርቻን ይሸፍናል።

15 ሄክታር መሬት በአረንጓዴ ተሸፍኗል። በውስጡም 210 ቀፎ ዘመናዊ ንብ እርባታ፣ የአበባ ጋርደን እና የእጽዋት ጋርደን የተካተቱበት ነው።

​የመሠረተ ልማት ግንባታዎች፦

​6.4 ኪሎ ሜትር የተሽከርካሪ መንገድ።

​8 ኪሎ ሜትር የሳይክል መንገድ።

​22 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ።

​4 ኪሎ ሜትር የሃይኪንግ መንገድ።

​39 ቼክ ዳሞች የተገነቡ ሲሆን፣ ሁለት አዳዲስ ድልድዮች እና ሶስት ነባር ድልድዮችም እድሳት ተደርጎላቸዋል።

​የከተማ አስተዳደሩ ይህንን ለብዙኃን አገልግሎት እንዲሰጥ ታሳቢ ተደርጎ የተገነባውን የከተማ መናፈሻ፣ የከተማው ነዋሪ እንዲጠቀምበት እና እንዲንከባከበው ጥሪ አቅርቧል። ፕሮጀክቱ ለመዝናኛ፣ ለንግድ እና ለተለያዩ ማህበራዊ ኩነቶች ምቹ ሆኖ የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል።





Leave a Comment