banner

የግብፅ እና የኤርትራ መሪዎች በካይሮ ተገናኙ፤ የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባህር ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ ሆኗል

​#FastMereja I የግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታህ ኤል-ሲሲ የኤርትራውን ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂን ዛሬ ሰኞ በካይሮ በይፋዊ የስራ ጉብኝት ተቀብለው አነጋግረዋል። መሪዎቹ በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታዎች እና በቀይ ባህር ፀጥታ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን የግብፅ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

​ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉብኝት፣ ፕሬዚዳንት ኤል-ሲሲ ግብፅ ለኤርትራ ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት የምታደርገውን ድጋፍ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ በበኩላቸው ከግብፅ ጋር ያለውን የምጣኔ ሀብት እና የንግድ ትብብር ይበልጥ ለማስፋት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረገው ይህ ከፍተኛ ውይይት፣ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ካለው ዲፕሎማሲያዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት አንጻር ቀጠናዊ ትኩረትን ስቧል።

Leave a Comment