0
#FastMereja I ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል። መንግስት በዘንድሮው የክረምት ወራት 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል እቅድ መያዙን ይፋ አድርጓል።
ይህ መርሃ-ግብር፣ ኢትዮጵያ በአምስት ዓመታት ውስጥ ለመትከል ካቀደችው 65 ቢሊዮን ችግኞች ግብ አንፃር የሚደረግ ወሳኝ አካል መሆኑ ተመላክቷል። አገሪቱ ባለፉት ዓመታት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርሰውን ተጽዕኖ ለመቀነስ እና የተፈጥሮ ሀብቷን ለመጠበቅ ዘመቻውን በስፋት እየተገበረች ትገኛለች።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልእክት፣ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሀገር አቀፍ ደረጃ በመሳተፍ ለቀጣዩ ትውልድ አረንጓዴ ዐሻራውን እንዲያኖር ጥሪ አቅርበዋል። መርሃ-ግብሩ የአካባቢ ጥበቃን ከማሻሻል ባሻገር፣ የኢኮኖሚ እና የብዝሃ-ህይወት ፋይዳ እንዳለው በመንግስት በኩል በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል።
