banner

ህፃን ወልዳ መቃብር ቦታ የጣለችው እናት የ6 ዓመት ከ3 ወር እስራት ተፈረደባት

​#FastMereja | በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ አዲስ የተወለደ ህፃን ወልዳ በመቃብር ቦታ በመጣል ለሞት የዳረገችው ወ/ሮ ዘርቱ ሃይሌ የ6 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራት ተቀጣች። ፍርድ ቤቱ ተከሳሿን በፈፀመችው የሰውን ልጅ ለአደጋ ወይም ለጉዳት በማጋለጥ ወንጀል ጥፋተኛ ብሎ የወሰነው ዛሬ ሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ነው።

​የይርጋጨፌ ከተማ ፖሊስ እንደገለጸው፣ አሳዛኙ ድርጊት የተፈጸመው ባለፈው ሚያዝያ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ ነው። ተከሳሿ በከተማዋ ካራ ቀበሌ ዶን ቦስኮ አካባቢ በሚገኘው ሙስሊም መቃብር ውስጥ አዲስ የተወለደውን ህፃን በመጣል ትታው የሄደች ሲሆን፣ በወቅቱ ህፃኑ በጉንዳን በመበላት ​የአካባቢው ነዋሪዎች የህፃኑን ለቅሶ በመስማታቸው ለፖሊስ ጥቆማ አድርገዋል። የፖሊስ አባላትም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ህፃኑን በፍጥነት ወደ ሆስፒታል በመውሰድ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ አድርጓል።

​የከተማዋ ፖሊስ ምርመራውን በማጠናቀቅ የክስ መዝገቡን ለሚመለከተው አካል ያስተላለፈ ሲሆን፣ የይርጋጨፌ ከተማ ችሎት የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 574/2ን በመጥቀስ ተከሳሿን ጥፋተኛ ብሎ በዛሬው ዕለት የ6 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራት ውሳኔውን አስተላልፎባታል።

#ችሎት

Leave a Comment