banner

የኢትዮጵያን የግብርና ምርታማነት ለማሳደግ ያለመ አዲስ የቴክኖሎጂ አማራጭ ይፋ ተደረገ

​#FastMereja I በኢትዮጵያ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የወጪ ንግድ ጥራትን ለመጠበቅ እና የአርሶ አደሩን ድካም ለመቀነስ የሰው ሰራሽ አስተዋጽኦ (AI) ቴክኖሎጂዎችን፣ ዘመናዊ የካሜራ ቁጥጥሮችን እና የከርሰ ምድር ሴንሰሮችን ያካተቱ አዳዲስ የግብርና መፍትሄዎች ወደ አገር ውስጥ እየገቡ መሆኑ ታውቋል።
​
​ጎልደን ላንድ ቶኩማ የተሰኘው የግብርና ቴክኖሎጂ ድርጅት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የሰብል ጤንነትን መከታተል የሚያስችሉ ክሮፕለር የቴክኖሎጂ ውጤት ወደ ኢትዮጵያ የግብርና ስርዓት ለማስገባት ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኘ ተነግሯል። ይህ ቴክኖሎጂ በአገሪቱ እየተተገበረ ያለውን የዲጂታል ግብርና ፍኖተ ካርታ እውን ለማድረግ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ታምኖበታል።

በተለይ ​በአገሪቱ የወጪ ንግድ ላይ ትልቅ ድርሻ ላላቸው እንደ ቡና እና የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ይህ አዲስ አሰራር፣ ሰብሎች ከመሬት ሳይነቀሉ በካሜራ እና በሳተላይት ድጋፍ በሽታዎችን ቀድሞ ለመለየት ያስችላል። ሰብሎችን በአካል የመጎብኘትና የመቆጣጠር ወጪን እስከ 40 በመቶ እንደሚቀንስ የተረጋገጠ ሲሆን፣ አርሶ አደሮችና ባለሀብቶች የተሻለ የውሳኔ አሰጣጥ ብቃት እንዲኖራቸው ይረዳል ተብሏል።

​ይህ የቴክኖሎጂ መፍትሄ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ22 በላይ አገራት ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ደግሞ በዋናነት ለትላልቅና መካከለኛ የንግድ እርሻዎች፣ ለቡና ላኪዎች፣ ለአግሮ-ኢንደስትሪዎች እና በተደራጁ የህብረት ስራ ማህበራት ስር ለሚገኙ አርሶ አደሮች ሰፊ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።





Leave a Comment