banner

የሙዝ ጫካ

#FastMereja I በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ በ482 አርሶ አደሮች በ435 ሄክታር መሬት ላይ በኩታ-ገጠም አሰራር የለማው የሙዝ ምርት፣ አካባቢውን ወደ ደንነት በመቀየር የተፈጥሮ ሥነ-ምህዳርን ከመጠበቁ ባሻገር የአርሶ አደሩን ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደገ መሆኑ ተገለጸ።

ይህ በደቡብ ቤንች ወረዳ የተመዘገበው ውጤት የክልሉን የሙዝ ምርት አቅም በእጅጉ ያጎላው ሲሆን፣ በክልል ደረጃ ከ73 ሺህ 785 ሄክታር በላይ መሬት በሙዝ በመሸፈኑ 13 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ ማቅረብ ተችሏል።





Leave a Comment