#FastMereja I በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የአነስተኛ የገንዘብ ኖቶች (በተለይም የ10 እና የ50 ብር ኖቶች) በከፍተኛ ሁኔታ መቀደዳቸው፣ ያረጁ መሆናቸው እና ከገበያ መጥፋታቸው በዕለት ተዕለት የንግድ እንቅስቃሴ እና ታክሲ አገልግሎት ላይ ከፍተኛ እንግልት እየፈጠረ ይገኛል።
እንደ ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ የሱቅ ባለቤት ህሩት አያሌው ያሉ በርካታ አነስተኛ ነጋዴዎች፣ የመልስ ገንዘብ በማጣታቸው ምክንያት ደንበኞቻቸውን በብድር ለማስተናገድ ወይም ምርታቸውን ሳያሸጡ ለመመለስ መገደዳቸውን ገልጸዋል። በገበያው ውስጥ የሚዘዋወሩት የ10 ብር ኖቶች ከጥቅም ውጪ እስከመሆን የደረሱና የተቀደዱ ሲሆን፣ ይህም በአገሪቱ እየታየ ያለው የዋጋ ንረት ገንዘብ በእጅ ወደ እጅ በፍጥነት እንዲዘዋወር በማድረጉ ምክንያት የመጣ አካላዊ መገለጫ እንደሆነ ይነገራል።
ችግሩን የባሰ ያደረገው ከባንክ ውጪ የሚዘዋወረው የገንዘብ መጠን በቢሊዮኖች የሚቆጠር መሆኑ እና የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ (Cashless System) ገና ሙሉ በሙሉ ባለመስፋፋቱ ነው የተባለ ሲሆን፣ የተቀደዱና ያረጁ ኖቶች ወደ ብሔራዊ ባንክ ተመልሰው በአዲሶች የመተካት ሂደታቸው ዘገምተኛ መሆን ክፍተቱን አሳድጎታል ሲል ፎርቹን ነው ያስነበበው።
