0
#FastMereja I በናይጄሪያ ዋና ከተማ አቡጃ በተካሄደ የሙስሊም ዓለም ሊግ ጉባኤ ላይ ከ50 በላይ የሙስሊም እና የክርስቲያን ሃይማኖት መሪዎች የጋራ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ።
ይህ በሁለቱ እምነቶች መካከል ያለውን እርስ በእርስ ውይይት እና ግንኙነት የሚያጠናክር የጋራ አካል ያቋቋመው ስምምነት፣ በሃገሪቱ ውስጥ በሁለቱም እምነት ተከታዮች ላይ ተጽዕኖ እያሳደሩ ያሉ የጥላቻ ንግግሮችን፣ ሃይማኖታዊ ትዕግስት ማጣትን እና ጽንፈኛ አመለካከቶችን ለመግታት ያለመ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
ከ200 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ናይጄሪያ በሰሜናዊው ክፍል አብዛኛው የሙስሊም፣ በደቡባዊው ክፍል ደግሞ የክርስቲያን ማህበረሰብ የሚኖርባት በመሆኗ ይህ ስምምነት ለሃገሪቱ ዘላቂ ሰላም እና አብሮነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
