#Fastmereja:- በጉራጊኛ ሙዚቃ ዘርፍ የሚታወቀው ድምፃዊ ተፈራ ፍቃዱ “ታውስማ” የተሰኘውን ሁለተኛ የሙዚቃ አልበሙን ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ሊያስመርቅ መሆኑን በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ አስታዉቋል።
በሰባት የተለያዩ ስቱዲዮዎች የተዘጋጀው ይህ አልበም፣ የጉራጌ ብሄረሰብ ሙዚቃን ጥራት ባለው መልኩ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በስራው ላይ እንደ ደምሴ ተካ፣ ደሳለኝ መርሻ፣ ፈለቀ ማሩ፣ አብራር ደሊል፣ ጎፈር፣ መስፍን ብርሃኑ እና ጋዜጠኛ ሙሉቀን ሀሰን ያሉ አንጋፋ ባለሙያዎች በግጥም እና ዜማ ተሳትፈዋል።
እንዲሁም በአቀናባሪነት አሌክስ ይለፍ፣ መሀመድ ኑርሴን፣ ዘሪሁን ሳህለማርያም፣ ኤርሚያስ ዘውዱ፣ ከድርሁሴን፣ በሀይሉ ዘርአይ እና ህስቅያስ ዘውዱ የተሳተፉበት ሲሆን፣ ታዋቂ ድምፃውያንን ያጀቡ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾች በቀጥታ (Live) ቅንብር ያጀቡት ሲሆን የአልበሙ አጠቃላይ ማኔጅመንት በአርቲስት ደሳለኝ መርሻ የተመራ መሆኑ ተገልጿል።
የምርቃት ስነ-ስርዓቱ ነሐሴ 24 ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ መካኒሳ አቦ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ እንደሚካሄድ ነዉ የተገለፀዉ።
በአልበሙ የምርቃት መርሃ-ግብር ላይ ሀይሉ ፈረጃ፣ ደሳለኝ መርሻ፣ ረሻድ ከድር፣ ፈለቀ ማሩ እና ኮሜዲያን አዝመራው ሙሉሰውን ጨምሮ 11 አርቲስቶች ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ በመግለጫዉ ተገልጿል።
አልበሙ በምርቃቱ ዕለት በድምፃዊው የዩቲዩብ ቻናል (Tefera.Fikadu) እና በዓለም አቀፍ የዲጂታል ፕላትፎርሞች ላይ ለህዝብ እንደሚደርስ ነዉ የተገለፀዉ።
#ኪነ_ጥበብ




