banner

የዓለማችን ፈጣኑ ሰው ዩሴን ቦልት ከ13 ዓመታት የፍቅር ቆይታ በኋላ ለካሲ ቤኔት የጋብቻ ጥያቄ አቀረበ

​#FastMereja I ስምንት የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያዎች ባለቤቱ እና የዓለማችን ፈጣኑ ሰው ዩሴን ቦልት ለረጅም ጊዜ አብራው ለዘለቀችው የህይወት አጋሩ ካሲ ቤኔት የጋብቻ ጥያቄ አቀረበ።

​ጃማይካዊ የሩጫ አትሌት የጋብቻ ጥያቄውን ያቀረበው በኪንግስተን ጃማይካ በተዘጋጀው የልደት በዓል አከባበር ስነ-ስርዓት ላይ በወዳጅ ዘመዶቻቸው ፊት ተንበርክኮ የ5 ካራት አልማዝ የጋብቻ ቀለበት በማሰር እንደሆነ ተገልጿል።

​እንደተረጋገጠው ሁለቱ ጥንዶች እ.ኤ.አ. ከ2013 ጀምሮ ላለፉት 13 ዓመታት በፍቅር አብረው የዘለቁ ሲሆን፣ የ6 ዓመቷ ኦሊምፒያ ላይትኒንግ እና የ5 ዓመት መንትያ ወንዶች ልጆች ታንደር እና ሴንት ሊዮ የተባሉ ሶስት ልጆችን አፍርተዋል።

​በስነ-ስርዓቱ ወቅት የ34 ዓመቷ ሞዴል እና ነጋዴ ካሲ ቤኔት የቀረበላትን ጥያቄ በደስታ የተቀበለች ሲሆን፣ የተደረገላት ሰርፕራይዝ እና የጋብቻ ጥያቄ ፈፅሞ ያልጠበቀችው እንደነበር ቅርብ ወዳጆቻቸው በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው አስፍረዋል።

Leave a Comment