0
#FastMereja I በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም የሚካሄደው «ግራንድ ኢሬቻ ቦክስ ምሽት» የቦክስ ውድድር በመጪው መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ምሽት እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታወቁ። ይህን ታሪካዊ ስፖርታዊ ዝግጅት በአፍሮ ኮ ትሬዲንግ እና ኤችኬ ኤንተርቴይንመንት ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት እንደሆነ ተገልጿል።
በዚሁ የስፖርት ምሽት ሰባት የወንዶች እና አንድ የሴቶች ውድድርን ጨምሮ በአጠቃላይ ስምንት የቦክስ ፍልሚያዎች ይካሄዳሉ። በውድድሩ ላይ የሚሳተፉት ተወዳዳሪዎች ከ48 እስከ 64 ኪሎ ግራም ክብደት ባላቸው የውድድር መደቦች የሚፋለሙ ሲሆን፣ ለዚህ ትልቅ ውድድር ላለፉት ዘጠኝ ወራት ያህል ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ተገልጿል። #ኹነት









