0
#FastMereja I ኢስት አፍሪካ ኢንተርቴይንመንት ኤንድ ኢቨንትስ በመስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል የሚካሄደውን የኢሬቻ በዓል ልዩ ዝግጅት አስመልክቶ አጠቃላይ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገለጸ።
በዕለቱ ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የተወጣጡ ታዋቂ አርቲስቶች የሚሳተፉበት ደማቅ ኮንሰርት የሚካሄድ ሲሆን፣ ጎን ለጎንም የ”ሚስ ዩኒቲ” የቁንጅና ውድድር እንደሚከናወን ተገልጿል። ለታዳሚዎች ምቹ የምግብ፣ የመጠጥ፣ የእረፍት ድንኳኖችና የትራንስፖርት አገልግሎት መመቻቸቱን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
የመግቢያ ትኬቶች በመደበኛ 1,000 ብር፣ በቪአይፒ (VIP) 10,000 ብር እና በቪቪአይፒ (VVIP) 20,000 ብር በቴሌብር እንዲሁም በየክፍለ ከተማው በሚገኙ ኤጀንቶች በመሸጥ ላይ ይገኛሉ። ከክልል ለሚመጡ ታዳሚዎች የትራንስፖርት አመቻች ኤጀንቶች የተዘጋጁ በመሆኑ ትኬት ሲገዙ መጠየቅ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።







