banner

አርቲስት ካሙዙ ካሣ በአዲስ አበባ ምክር ቤት ቃለ መሃላ ፈጸመ

#FastMereja I ​የሙዚቃ እና የኪነ ጥበብ ባለሙያው ካሙዙ ካሣ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከአዲስ አበባ ሕዝብ የተሰጠውን ውክልና በመቀበል፣ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ፊት ቀርቦ የቃለ መሃላ ስነ ሥርዓት ፈጽሟል።

​አርቲስቱ ከቃለ መሃላ ስነ ሥርዓቱ በኋላ ባስተላለፈው መልዕክት፤ መራጩ ሕዝብ የሌሊት ብርድና የቀን ሐሩር ሳይበግረው ውክልና እንደሰጠው ገልጾ፣ የተጣለበትን የሕዝብ አደራ በታማኝነት፣ በቅንነት እና ያለ አድልዎ ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።

​በቀጣይም ለሕዝቡ ባስገባው ቃል መሠረት ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ፣ በተለይም በሥራ ፈጠራና በኪነ ጥበብ ዘርፎች ከተማዋንና ኢትዮጵያውያንን በሚመጥን መልኩ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጿል።










Leave a Comment