banner

በደቡብ ወሎ ድንገተኛ የእሳት አደጋ 56 ቤቶች ወደሙ

#FastMereja I በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ 18 ቀበሌ «ምስትንክር» በተባለ ጎጥ በተከሰተ ድንገተኛ የእሳት አደጋ 56 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገለጸ። ከተቃጠሉት ቤቶች መካከል 52ቱ የሳር እንዲሁም 4ቱ የቆርቆሮ ክዳን ያላቸው መሆናቸው ታውቋል።

በዚህ ድንገተኛ አደጋ የ30 አበወራ እና እማወራ አባላት የሆኑ 171 የህብረተሰብ ክፍሎች የጉዳቱ ሰለባ ሆነዋል። ከቤቶቹ ውድመት በተጨማሪ 348 ኩንታል እህል፣ የቤት እንስሳት እና ሙሉ የቤት እቃዎች በእሳቱ መቃጠላቸው ተረጋግጧል።

የወረዳው አደጋ ስጋት ስራ አመራር ቡድን በአደጋው ምክንያት ለተጎዱትና መጠለያ አልባ ለሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች አስቸኳይ የድንገተኛ እርዳታ እንዲደረግ የደላንታ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጥሪ አቅርቧል።





1 comment

ብርሃን ለአለም መብራት October 11, 2026 - 1:11 pm

ዲቃላው ፋኖ የሰራው ስራ ነው።

Reply

Leave a Comment