banner

የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አድናቆት አተረፈ

#FastMereja I ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን አስመልክቶ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ከፍተኛ አድናቆታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ። አብዛኛዎቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በተወሳሰበ አሰራር እና በእንቅስቃሴ መዘግየት በሚታሙበት በዚህ ወቅት፣ መሶብ የሚሰጠው የተቀላጠፈ እና ዘመናዊ አገልግሎት አርአያነት ያለው መሆኑን አገልግሎቱን ያገኙ ዜጎች ገልጸዋል።

የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በሰጡት አስተያየት፣ በማዕከሉ የሚያጋጥማቸው ፈጣን አስተናጋጅነት እና ቅንጅታዊ አሰራር የሚያስመሰግን መሆኑን ጠቅሰው፤ ተቋሙ የጀመረውን ጥራት ያለው አገልግሎት አጠናክሮ እንዲቀጥል እና ሌሎች የመንግስት ተቋማትም ይህንን አሰራር አብነት አድርገው እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህንን በሀገር አቀፍ ደረጃ ትልቅ ትኩረት ያገኘውን የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየመራ የሚገኘው ወጣቱ አመራር ዮናስ አለማየሁ እንደሆነ ታውቋል። ዮናስ ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ውስጥ ባሳየው የላቀ የአመራር ብቃት እና አሰራርን በማዘመን ሂደት ያስመዘገበውን ስኬት፣ አሁን ደግሞ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ላይ በድጋሚ እያሳየ ይገኛል።

1 comment

Bethani Ahmed October 25, 2026 - 9:29 am

Good self promotion

Reply

Leave a Comment